ኢትዮጵያ በቻይና በተካሄው ዓለም ዓቀፍ ልዩ የቡና ትርዒት ላይ ተሳተፈች

ኢትዮጵያ በቻይና ፑኤር ከተማ በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ ልዩ የቡና ትርኢት ላይ ተሳትፋለች።

የዓለም አቀፍ የቡና ትርዒቱን የቻይና የንግድ ሚኒስቴር እና የዩና ግዛት ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ቢሮ  በጋራ አዘጋጅተውታል።

በትርዒቱም ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ፣ ልዩ ጣዕምና ጥራት እንዲሁም በርካታ የቡና አይነቶችን ለዓለም በተለይም ለቻይና ህዝብ ማስተዋወቅ መቻሉ ነው የተገለፀው።

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተመራጭ መሆኑና በቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እያደገ መምጣቱ ተገልጿል።

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጥሬ ቡና የሚልኩ ሀገራት እሴት በመጨመር ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስቸሉ ልምዶችም ቀርበዋል።

ከትርኢቱ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ልዑክ ከፑኤር ከተማ ከፍተኛ ሃላፊዎችና የዩና ግዛት ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ቢሮ ተወካዮች ጋር በዘርፉ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በፕሮግራሙ ላይ ቡና በማቀነባበር፣ በማልማት፣ በማምረት፣ በመሸጥና ተያያዥ ዘርፎች የተሰማሩ ከ1ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር