የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል ቀጥታ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል የቀጥታ በረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ከሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል በሳምንት 3 ቀናት ይበራል ነው የተባለው፡፡

ኢስታንቡል የቱርክ ታሪካዊ፣ የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ከተማ እንደሆነች ይነገርላታል፡፡

የኢስታንቡሉ ቀጥታ በረራ የአውሮፓ 19ኛው መዳረሻው ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ በአምስቱም አህጉራት 119 መዳረሻዎች አሉት፡፡ (ምንጭ፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ)