የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኒዮርክ ታይምስ ዘገባ ቅሬታዉን ገለፀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መከስከስን አስመልክቶ በሰራዉ ዘገባ ላይ ቅሬታዉን ገለፀ፡፡

አየር መንገዱ ጋዜጣዉ “አብራሪዎቹ የሲሙሌተር ስልጠና አልወሰዱም” ብሎ መዘገቡ ስህተት መሆኑን ገልጿል፡፡

የአየርመንገዱ አብራሪዎች  ይህን አዉሮፕላን ለማብረር የሚያስችለዉን በአሜሪካዉ የፌዴራል የበረራ አስተዳደር የፀደቀዉን ስልጠና መዉስዳቸዉን አየርመንገዱ በመግለጫዉ አስታዉቋል፡፡

እንደ አየርመንገዱ ገለጻ አብራሪዎቹ ከላየን አየር መንገድ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ ከደረሰበት በኃላ በአደጋ ጊዜ ምንማድረግ እንዳለባቸዉ የሚያስረዳ ስልጠና ወስደዋል፡፡

የአደጋዉን መንሰኤ ተጣርቶ አስከሚታወቅ ድረስ ሁሉም የሚመለከተዉ አካል ከተሳሳተ እና ኃላፊነት ከጎደለዉ መግለጫ ተቆጥቦ በትግስት እንዲጠብቅ አየርመንገዱ አሳስቧል፡፡