ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሐረር፣ ቦምባሥና ጭናግሰን የሚባሉ አካባቢዎች ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከል በኮንትሮባድ መንገድ የገቡ አልባሣት እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንደሚገኙባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

እቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በኦሮሚያ የአድማ በታኝ ፖሊስ፣ ጉምሩክ ሠራተኞች እና መከላከያ ሰራዊት አባላት ትብብር ነው ተብሏል፡፡

(ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር)