የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 504 ቢሊየን ብር ደረሰ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 504 ቢሊየን ብር መድረሱ ተገለፀ።
ባንኩ ሰሞኑን በአዳማ ከተማ የ9 ወር ሪፖርት የዕቅድ አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡
የባንኩ ሥራ አስፈፃሚና ፕሬዚደንት አቶ ባጫ ጊና እንደገለጹት ሕብረተሰቡ ስለ ቁጠባ ያለውን ግንዛቤ እና ባህል ማሳደግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በመሠራታቸውና የተቀማጭ ሀብት ማሰባሰብ ስትራቴጂ ተግባራዊ በመደረጉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 52 ቢሊየን ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

የውጭ ምንዛሬ ከማሳደግ ረገድም ባለፉት 9 ወራት 4 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰብ መቻሉን አክለው ገልጸዋል፡፡

(ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)