የኢትዮ-ሱዳን የቢዝነስ ፎረም ተጀመረ

የኢትዮ ሱዳን ቢዝነስ ፎረም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

ፎረሙ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስና ዳያስፖራ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ደዋኖ ከድር በተገኙበት ነው በይፋ ተከፍቷል፡፡

በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በማጠናከር እንዲሁም ባለሀብቶች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦችን ማመላከት የቢዝነስ ፎረሙ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን አምባሳድር ደዋኖ ከድር በመክፈቻው ላይ ገልጸዋል።

ይህ ፎረም ካርቱም በሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲ እና አዲስ አበባ በሚገኘው የሱዳን ኤምባሲ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሁለቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ፎረሙን በማስተባባር ተሳትፈዋል።

በፎረሙ ላይ ከ100 በላይ ታዋቂ የሱዳን እና የአትዮጰያ ባለሀብቶች እንዲሁም የኩባንያ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ፎረሙ በዛሬ ውሎው የሁለቱን አገሮች የኢኮኖሚ ትብብር፣ የንግድ ትስስስር እንዲሁም ግንኙነኙነቱን ይበልጥ ለማሳለጥ በሚያስችሉ ርዕሶች ላይ በሚቀርቡ ጽሁፎች ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

የባለሀብቶች የአንድ ለአንድ ውይይትም ዛሬ ከስዓት በኋለ የሚካሄድ ሲሆን፣ የፎረሙ ተሳታፊዎች በነገው እለት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚጎበኙም ተፀቁመዋል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት)