የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የተጓዥ ደንበኞችን በማፍራት ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይናው ቻንጋይ አየር መንገድ ቡድን ባዘጋጀው በ2019 በመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቀጠና ከፍተኛ የተጓዥ ደንበኞችን በማፍራት ሽልማት አሸነፈ፡፡

አየር መንገዱ መረጃውን በትዊተር ገፁ አስታውቋል፡፡

በሽልማት ዝግጅቱ ላይ ሌሎች አየር መንገዶችም በተለያዩ ምድቦች አሸንፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ ከ120 በላይ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንትም ከአፍሪካ አየር መንገዶች ውስጥ ምርጡ የጭነት አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በሚል ለ4ኛ ጊዜ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡