ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 2.9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የአሜሪካ ገቢ ተገኘ

ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 2.9 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የአሜሪካ ገቢ ተገኘ

በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 2 ነጥብ 39 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ገቢው የተገኘው በበጀት ዓመቱ ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ እና ከማዕድን ምርቶች ዘርፍ ሲሆን፤ አፈጻጸሙ የእቅዱን 61 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

አፈፃፀሙም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 2.59 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ 7.61 በመቶ ቅናሽ  አሳይቷል፡፡ የእቅድ አፈጻጸሙን ለማሻሻል በቀጣይ ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ርብርብ እንደሚደረግ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።