ኤጀንሲው የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን አካላት ሊሸልም መሆኑን ገለፀ

የፌዴራል የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ካሉት 1ሺህ 700 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡትን ሰኔ 25፣ 2011 ዓ.ም ሊሸልም መሆኑን ገለፀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ እንደተናሩት 78 ማዕከላት እና 275 ባለሙያዎች በውጤታማ አፈፃፀማቸው እውቅናና ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡

በእውቅና መስጠት መርሃ ግብሩ ለተሸላሚ ማዕክላት የቢሮ እቃዎች የሚበረከትላቸው ሲሆን ለባለሙያዎች ደግሞ የትምህርት እድል እና ሌሎች የማትጊያ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

የኤጀንሲው የአንድ መስኮት አገልግሎት ጣቢያዎች ዜጎች የሚፈልጓቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች እንግልት ሳይገጥማቸው በአንድ ቦታ ላይ እንዲያገኙ ታስበው የተመሰረቱ ናቸው ብለዋል ፡፡