ኮካኮላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቱ ላይ የ300 ሚሊየን ዶላር ማስፋፊያ ሊያደርግ ነው

ኮካኮላ በኢትዮጵያ ባለው ኢንቨስትመንት ላይ የ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማስፋፊያ ሊያደርግ መሆኑ ተገለፀ።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ባለው ኢንቨስትመንት ላይ የሚያደርገው የ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማስፋፊያው በ5 ዓመታት ውስጥ የሚተገበር መሆኑም ተገልጿል።

በማስፋፊያውም በመጀመሪያ ዙር ከአዲስ አበባ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰበታ ከተማ አራተኛ የኮካኮላ ምርቶች ፋብሪካ ግንባታ እንደሚያከናውን ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

በሰበታ የሚገነባው ፋብሪካው በ70 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚደረግበት መሆኑንም የኮካኮላ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ፍራንቻይዝ ማናጀር በሩኖ ፒቴራሲን በምጠጥቀስ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ኤምባሲ አስታውቋል።

በሰበታ ከተማ የሚከናወነው 4ኛው የኮካኮላ ፋብሪካ ግንባታ ሲጠናቀቅም በቀን እስከ 70 ሺህ ካሳ የኮካኮላ ምርቶችን በመሙላት ለገበያ የሚያቀርብ መሆኑም ተጠቅሷል።

ኮካኮላ 5ኛ የኮካኮላ ምርቶች ፋብሪካውን ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ለመገንባት እቅድ እንዳለውም ነው የኩባንያው መግለጫ የሚያመላክተው መረጃዉ ፊን24ዶትኮም ዘግቧል።