ኩዊንስ ሱፐርማርኬት 7ኛ ቅርንጫፉን በኮልፌ ቀራንዮ አስመረቀ

በሚድሮክ ኩባንያ ስር የሚገኘው ኩዊንስ ሱፐርማርኬት 7ኛ ቅርንጫፉን በኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ ዛሬ አስመርቋል፡፡

ሱፐርማርኬቱ እጅግ ዘመናዊና ለግብይት አመቺ መሆኑን  ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቱቭ ኦፊሰርና የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገልፀዋል፡፡

ቅርንጫፉ ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል የተሽከርካሪ ማቆሚያን ያሟላ እና ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ዓመታዊ ሽያጭን አመታዊ ሽያጭን እንደሚያከናውንም ዶ/ር አረጋ ተናግረዋል፡፡

ተመሳሳይ ቅርንጫፎችን በየአካባው ለመክፈት መታቀዱም በምረቃው ወቅት ተገልጿል፡፡