የገቢዎች ሚኒስቴር በነሃሴ ወር ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር በዘንድሮ በጀት አመት በሰራቸዉ የንቅናቄ ስራዎች፣ የህግ ማስከበር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የህግ ማሻሸያ ስራዎች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ።

ሚኒስቴሩ በወሩ 19 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ  ከ20 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

ይህም የዕቅዱ 102 ነጥብ 37 በመቶ ሆኗል።

15 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ከተሰበሰበበት አምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም 2የ5 ነጥብ 45 በመቶ ብልጫ አለው።

ይህ ዉጤት ሊመዘገብ የቻለዉ ግብር ከፋዩ በታማኝነት ግብሩን በአግባቡና በወቅቱ መክፈል በመጀመሩና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በቅንነትና ተገቢዉን አገልግሎት በመስጠታቸዉ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

በቀጣይም አመታዊ እቅዱ እንዲሳካ እና አገራዊ ገቢን የማሳደግ ራዕይ እዉን እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አሳስቧል፡፡

ሚኒስቴሩ በበጀት አመቱ 248 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ  አቅዷል።