የኢሬቻ ባዛር እና ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ

የኢሬቻ ባዛር እና ኤግዚቢሽን የአሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በተገኙበት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።

በዛሬው ዕለት የተከፈተው ባዛር እና ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዴ በመስከረም 24 እና 25 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም የተለያዩ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ሲሆን፣ የኢሬቻ ባህላዊ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከእነዚህ ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።