በጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፤ በጥቅምት ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር ሁሉም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የአውሮፕላን ነዳጅ በመስከረም ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር ብር 25.56 በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት፤ 1 ብር ከ 07 ሳንቲም በመጨመር በሊትር ብር 26.63 እንዲሸጥ ተወስኗል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊያደርግ እንደሚችል ነው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያስታወቀው።