ማንኛውም ሰው የሚመገባቸውን የምግብ አይነቶች በመምረጥና አግባብነት ያላቸውን የአመጋጋብ ዘዴዎች በመከተል ረጅም እድሜ የወጣትነት ገጽታን ጠብቆ መቆየት እንደሚችል በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ሳይንቲስቶች ገለጹ ።
ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመከተል ሰዎች ክብደታቸውን እንዲቀንሱ በማድረግና የወጣትነት ገጽታን የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ በየዕለቱ የምንወስደውን የካሎሪ መጠንን መቀነስ የጎመን ሾርባ ለምግብነት መጠቀም እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ተመልክቷል ።
የተለያዩ የሞሎውኪላር ስነ -ህይወት ተመራማሪዎችና የጤና ስነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙተ ተገቢ ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ያለመውሰድ እጅግ ጠቃሚ መሆኑንና የውስጥና የውጭ የሰውነት አካል እንዳያረጅ የሚያደርጉ ሁኔታዎች እንደሆኑ ገልጸዋል ።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በውጫዊ የሰውነት አካል ላይ እርጅናን ከሚያመላክቱ ሁኔታዎች ዋናዎቹ መካከል በቆዳ ላይ የሚወጡ መስመሮች፣ የፀጉር መሸበት ፣ድካምና ህመሞች ሲሆኑ በሁሉም የሰውነቶታችን ክፍሎች ላይ የሚገኙ ህዋሳትን ስለ ማርጀታቸው የሚቆጣጣረው የዘር ቅንጣት ወይም ክሮሞሶም መሆኑ ተመልክቷል ።
የማንኛውም የሰው የዘር ቅንጣት በረዘመ ቁጥር የሰውነት ህዋሶች እንዳያረጁና ለበሽታ እንዳይጋለጡ በማድረግ ሰዎች የወጣትነት ገጽታን እንዲላበሱና ደስተኛ እንዲሆኑ የማድረግ አቅም ይኖረዋል ።
እርጅናን የሚያፋጥኑ ምግቦችና መጠጦች
• ቀይ ሥጋ
•ነጭ ዳቦ
• ጣፋጭ መጠጦች
• ከፍተኛ ስብ ያላቸው ምግቦች
• የኑግ ዘይት ፣ የሱፍ ዘይትና ጤናማያልሆኑ ብስኩቶች
• አልኮኖች ናቸው ።
ወጣትነትን የሚያላብሱ የምግብና የመጠጥ አይነቶች
• የጥራጥሬ ምግቦች በሙሉ
• ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶችናሥራ ሥሮች
• አደንጓሬ ፣ ለውዝና አብሽ
• የአሳ ሥጋ
• የዶሮ ስጋ ( ከኦርጋኒክ ነጻ የሆነ)
• አረንጓዴ ሻይና
• ቡና ናቸው ።
(ምንጭ: ቢቢሲ)