ባደጉ አገራት የሰው አማካኝ እድሜ ከ90 ዓመት በላይ እንደሚሆን ተመለከተ

ባደጉ አገራት የሰው ልጅ አማካኝ የመኖር ዕድሜ እኤአ በ2030 ከ 90 ዓመት በላይ እንደሚሆን ጥናት ጠቆመ

በእንግሊዝ የለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር  በመተባባር  በ35 ያደጉ አገራት ላይ  በሠራው ጥናት እንዳስታወቀው  እኤአ  በ2030  የሰው ልጅ  ረጅም እድሜ የመኖር ዕድሉ እየሰፋ ይመጣል ።

በተለይ  የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው ለወደፊቱ በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለው አማካኝ የዕድሜ ልዩነት  እየጠበበ  እንደሚመጣ  ገልጸዋል ።    

የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው በእድሜ የገፉ ሰዎችን ለመንከባከብ  የሚውለው ገንዘብም በየአገራቱ   እየጨመረ እንደሚመጣ ተገልጿል ።

የደቡብ ኮሪያ  ሴቶች በአማካኝ 90  ዓመት  ለመኖር  ቀዳሚ እንደሚሆኑ  የጠቆመው ጥናቱ ደቡብ ኮሪያ ብዙ ነገሮችን   በትክክል እያካሄደች በመሆኑ ረጅም ዕድሜ የመኖር የተሻለ እድል ለወደፈቱም እንደሚኖራት ዶክተር ማጂድ ኢዛቲ ለቢቢሲ  ተናግረዋል ።

በደቡብ ኮሪያ  አብዛኛው ህዝብ የትምህርት ዕድል የሚያገኝና የምግብ ዋስተናውም የተረጋገጠ ከመሆኑን በላይ በኑሮው ላይ ውጥረት  ባለመኖሩ ምክንያት   በዓለም ላይ  ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ከመጠን በላየ ውፍረት ያላቸው ሰዎች የሚገኙባት መሆኗን ጥናቱ አብራርቷል ።

በአሁኑ ወቅት ጃፓን ረጅም እድሜን የሚኖሩ ብዛት ያላቸው ሰዎች የሚገኙባት አገር ብትሆንም  ለወደፊቱ  ደረጃዋን በደቡብ ኮሪያና ፈረንሳይ  እንደምትነጠቅ ትንታኔ ያቀረበው  ጥናቱ  በተለይ  በወንዶች አማካኝ እድሜ እርዝማኔ  ወደ 11ኛ ደረጃ እንደምትወርድ ተገልጿል ።   

አሜሪካ   እኤአ በ2030  ረጅም እድሜ በመኖር  ደረጃ  ካደጉት አገራት የመጨረሻውን ሥፍራ ይዛ  እንደምትቀጥል  ተመልክቷል ።  የአሜሪካ  ከሜክሲኮና ከክሮሺያ  በተመሳሳይነት  አማካኝ የወንዶች የእድሜ ጣሪያ  80 የሴቶች ደግሞ  83   ሆኖ ለወደፊቱ እንደሚጠቅል ጥናቱ አመላክቷል ።

( ምንጭ : ቢቢሲ)