የለሊት ሽንት መብዛት ከጨዋማ ምግብ ጋር እንደሚያያዝ ተመለከተ

ሌሊት  በተደጋጋሚ በሽንት  ምክንያት  እንቅልፍን  የማቋረጥ ሁኔታን ለመከላከል   ጨዋማ  ምግቦችን   መቀነስ  እንደሚገባ  የጃፓን ዶክተሮች   አመለከቱ ።

በተለይ  ከ 60 ዓመት  በላይ የሚገኙ አዛውንቶች   ለሊት  በእንቅልፍ ወቅት  በተደጋጋሚ ለሽንት   የመነሳት ሁኔታና  የእንቅልፍ መዛባት  ይታይባቸዋል ።

ከ 300  በላይ  ፈቃደኞችን ላይ  የጃፓን ተመራማሪዎችና የጥናት  ባለሙያዎች  ያደረጉት  ጥናት እንደሚያሳየው  ሰዎች  በሚወስዱት ምግብ ውስጥ ያለውን የጨው  መጠን በቀነሱ ቁጥር  የሸንት መጠናቸውም ይቀንሳል ።         

የመመገብ ልማድ ያላቸውና  የእንቅልፍ መቆራረጥ ችግር ያለባቸውን  ሰዎችን በመለየት  ለሶስት  ወር ክትትል  በማካሄድ  በምግባቸው ውስጥ  የሚጠቀሙትን የጨው  መጠን እንዲቀንሱ  ምክር  ከተሠጣቸው  በኋላ የእንቅልፍ መቆራረጥ  ችግራቸውና  ለሽንት የመነሳት ጊዚያቸው መቀነሱ ታይቷል ። 

ዶክተር  ሙታሶ ቶማሂሮ እንደገለጹት የጨው መጠን መቀነስ  ለብዙ ሰዎች   በተለያየ መልክ  የቀንንና የለሊት ህይወት  የተሻለ ለማድረግ  ይረዳል  ጫናንም ይቀንሳል  ።( ምንጭ : ቢቢሲ)