በአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች አውሮፕላኖች በሚነሱበት ወቅት በሚፈጥሩት ድምጽ ብክለት ምክንያት 86 በመቶ ለስኳር በሽታ ቁጥር ሁለት የመጋለጥ ዕድልን እንደሚጨምር በዘርፉ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ሳይንቲስቶች ገለጹ ።
ሳይንቲስቶቹ እንደሚናገሩት አውሮፕላን በሚያኮበኩብበት ወቅት የሚያወጣው ድምጽ ከአየር ብክለት በበለጠ ሁኔታ በሰዎች ሰውነት ላይ የተለያዩ ሆርሞኖች እንዲብላላ በማድረግ የደም የስኳር መጠን እንዲያደግ ያደርጋል ።
በተለይ በእንቅልፍ ሰዓት አውሮፕላን ድምጽ እንቅልፍን ከማስተጓጎልም በላይ በአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ነዋሪዎች ድምጹን ለመከላከል መስኮታቸውን መዝጋት ይጠበቅባቸዋል
።
አውሮፕላኖች በሚነሱበት ወቅት የሚያስወጡት ድምጽ በሰው ልጅ ላይ አዕምሮ ላይ ውጥረትን የመፍጠር ሃይል እንዳለው የሚያስረዱት ሳይንቲስቶቹ የድምጽ ብክለቱ ለቁጥር ሁለት የስኳር በሽታ መንስኤ ከመሆኑም ባሻገር ለልብ፣ ለስትሮክና ለተለያዩ በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል ።
በእንግሊዝ ለአውሮፕላን ድምጽ ብክለት የተጋለጡ ሰዎች ከ3 ሚሊዮን የማያንሱ መሆናቸውንና ለህምክናም በቀን 2ነጥብ 2 ሚሊዮን ፓውንድ ለህክምና ወጪ እንደሚጠይቅ ተገምቷል ።
ቀደም ሲል የአውሮፓ ህብረት ባወጣው መረጃ መሠረት በእንግሊዝ ሂትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ ከ700ሺ በላይ ሰዎች ለድምጽ ብከላ የተጋለጡ ሲሆን በተለይ 2ሺ 600 የሚደርሱ ሰዎች ለይ ባካሄደው ጥናት የድምጽና የአየር ብከላው ሰለባ መሆናቸው ተረጋግጧል ።
የዓለም አቀፉ የኢፒዲሞሎጂ ጆርናል ዋና አዘጋጅ ዶክተር ማያናክ ፓቴል እንደሚገልጹት ጥናቱ በድምጽ ብክለትና በስኳርና በሽታ መካከል ያለውን ግንኙነት በጉልህ ያሳየ ነው ብለዋል ።