መድሃኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታን ማጥፋት ተግዳሮት መሆኑ ተገለጸ

የቲቢ በሽታን ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት መድሃኒቱን የተላመደ በሽታ ተግዳሮት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው እ.ኤ.አ በ2017 ዓ.ም 600 ሺህ ያህል መድሃኒቱን የተላመደ የቲቢ በሽታ ህሙማን ተመዝግበዋል፡፡ 

ከእነዚህ ህሙማን መካከል 82 በመቶ ያህሉ በሽታቸው የተለያዩ የቲቢ በሽታ መድሃኒቶችን የተላመደ ሆኖ መታየቱ ተነግሯል፡፡

መድሃኒቱን ለተላመደ የቲቢ በሽታ ከተጋለጡ አራት ህሙማን አንዱ መደሀኒቱን የተላመደ የቲቢ ህክምና ክትትል የሚያደርግ ሲሆን የህሙማኑ ከዚሁ በሽታ የመፈወስ እድል 55 በመቶ ያህል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

10 ሚሊዮን ያህል ሰዎች በቲቢ በሽታ የሚሰቃዩ ሲሆን በየዓመቱ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች በዚህ በሽታ ሕይወታቸው ያልፋል ተብሏል፡፡