ጠ/ሚ ዐብይ በመጪው ቅዳሜ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ይወያያሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመጪው ቅዳሜ ከ3ሺህ የጤና ባለሙያዎች ጋር እንደሚወያዩ ተገለጸ፡፡

ከ3 ሺህ የጤና ባለሙያዎች እና 1 ሺህ የሚሆኑ ተሳታፊዎች በኦን ላይንና በስልክ በፈቃደኝነት እየተመዘገቡ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ከተሳታፊዎች መካከል 1 ሺህ የሚሆኑት ከክልሎችና ከሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የጤና ተቋማት ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 1ሺህ የሚሆኑት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከሙያ ማህበራትና ከግል የጤና ተቋማት እንደሚሆኑም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በኦንላይንና በስልክ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ዝርዝራቸው በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገጽ እና በፌስ ቡክ ገጽ እንደወጣና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ አርብ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት በጤና ሚኒስቴር በመገኘት የመግቢያ ባጅ መቀበል እንዳለባቸውም አሳስቧል፡፡

ውይይቱም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሠብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል ነው የተባለው፡፡

(ምንጭ፡- የጤና ሚኒስቴር)