72ኛው አለም አቀፍ የጤና ጉባኤ በጄኔቫ እየተካሄደ ነው

72ኛው አለም አቀፍ የጤና ጉባኤ በጄኔቫ ስዊዘርላንድ መካሄድ ጀመረ፡፡

በኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጉባዔው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በገባኤው ኢትዮጵያ ሁለት ለውሳኔ የሚቀርቡ አዳዲስ ሀሳቦችን እንደምታቀርብ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መራጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ በሚገኘው 72ተኛው የጤና ዓለም አቀፍ ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

 በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከጉባዔው ጎን ለጎን የሚካሄዱ ሁለት ስብሰባዎችን በማዘጋጀት ትመራለች ተብለዋል።

የልዑካኑ ቡድኑ ከሌሎች ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ እና አዳዲስ ትብብሮችን ለመፍጠር ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል።