የኢትዮጵያ የወባ በሽታ የማጥፋት ጥረትን የአሜሪካኑ ድርጅት እንደሚደግፍ ገለጸ

ኢትዮጵያ የወባ በሽታን ለማጥፋት እያደረገች ላለው እንቅስቃሴ የአሜሪካን ፕሬዚደንት የወባ ኢኒሼቲቭ (PMI) ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚደንት የወባ ኢኒሼቲቭ (PMI) አለም አቀፍ የወባ እስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ኬኔት ስታሌይ በ72ኛው አለም አቀፍ የጤና ጉባኤ ላይ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የወባ በሽታን ለማስወገድ የጀመረችውን እንቅስቃሴ አድንቀው የአሜሪካ ፕሬዚደንት የወባ ኢኒሼቲቭ (PMI) ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

(ምንጭ፡- ጤና ሚኒስትር)