የፅንስ ክትትል ለማድረግ የሚረዱ 3ሺህ 600 ዘመናዊ መሳሪያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊሰራጩ ነው

የነፍሰ ጡር እናቶችንና የፅንስ ክትትል ለማድረግ የሚረዱ 3 ሺህ 600 ዘመናዊ መሳሪያዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት ሊጀመር ነው።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅቦት ኤጀንሲ 3ሺህ 600 የሚሆኑ የነፍሰ ጡር እናቶች እና የፅንስ ክትትል ለማድረግ የሚረዳ ዘመናዊ መሳሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሆስፒታሎች እና ለጤና ጣቢያዎች ለማከፋፈል ዝግጅቱን አጠናቋል።

በቅርቡም መሳሪያዎቹ ለታለመላቸው አላማ ይውሉ ዘንድ ለተመደቡበት ሆስፒታልና ጤና ጣቢያ የሚከፋፈሉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ተናግረዋል።

ይህም የእናቶች እና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል መረጃዉ ኤፍቢሲ ነዉ።