ኢትዮጵያ በአፍሪካ በትንባሆ እና አልኮል ላይ ጠንካራ ህግ ካወጡ ስድስት አገራት መሀል አንዷ ሆነች

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትንባሆ እና አልኮል ቁጥጥር ላይ ጠንካራ ህግ ካወጡ ስድስት አገራት መሀል አንዷ በመሆኗ ዕውቅና ተሰጣት፡፡

የአለም የጤና ድርጅት በአፍሪካ ትንባሆ እና አልኮል ቁጥጥር ላይ ጠንካራ ህግ ካወጡ ስድስት አገራት መሀል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጾ ይህን አዋጅ ቁጥር 1112/2011(የምግብና መድኃኒት አስተዳደር) ላፀደቀው የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እውቅና ሰጥቷል::

ህጉንም ተግባራዊ በማድረግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ’ከትምባሆ ጭስ ነጻ’ መሆኑን አውጇል::

ይህም በሌሎች የፌደራል እና የክልል ተቋማት ላይ ተፈፃሚ እንዲሆን ከተቆጣጣሪ ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን ክትትል እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል::

አዲሱ የምግብ እና የመድኅኒት አስተዳደር አዋጅ አንቀጽ 48፣1 የተቀመጠውን ድንጋጌ ከበር መልስ ባሉ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ማጨስን ይከለክላል እንዲሁም በህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ትንባሆ የማጨስ ክልከላን በተመለከተ ግልጽ እና ጎላ ያሉ ማስታወቂያዎች መቀመጥ እንዳለበት አስቀምጧል፡፡/የጤና ሚኒስቴር/