ህብርተሰቡ የፓልም ዘይትን በተመጠነ መልክ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ

ህብርተሰቡ ለምግብነት የሚጠቀመውን የፓልም ዘይት በተመጠነ መልኩ መጠቀም እንደሚገባው የኢትዮጵያ ህብርተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

ኢንስቲትዩቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ከዚህ ቀደም ከውጭ የሚገባውን ፓልም ዘይት እና ሌሎች በሀገሪቱ የሚመርቱ ዘይቶች ደርጃቸውን ጠብቀው እንዲመረቱ በሚል የጥናት ውጤት ማሳወቁን አስታውቋል።

ሆኖም በወቅቱ ህብርተሰቡ ጋር የደርሰው መረጃ መደናገርን መፍጠሩን ገልጾ፥ ህብርተሰቡ የፓልም ዘይትን እንዳይጠቀም ሳይሆን በተመጠነ ምልኩ እንዲጠቀም ነው መልዕክቴን ያስተላለፍኩት ብሏል።

በቀጣይም ከአጠቃቀም ጋር ተያይዞ ሊደርጉ ይገባል ያላቸውን ጥንቃቄዎችን ገልጿል።

በተለይም ሰውነት ከሚያቃጥለው በላይ ይህንን ዘይት ሰዎች የሚጠቀሙ ከሆነ የደም ቧንቧ ላይ እየተጋገረ እንደሚመጣ ያነሳው ተቋሙ፥ አጠቃቀማችን የተመጠነ መሆን አለበት ሲል አሳስቧል።