በህፃናት ምግብ ውስጥ የሚኖረው የስኳር መጠን አነስተኛ መሆን እንደሚገባ ጥናት አመላከተ

በህፃናት ምግብ ውስጥ የሚኖረው የስኳርና ቅባት መጠን አነስተኛ መሆን እንደሚገባ አንድ ጥናት አመላከተ።

ሰሞኑን በብሪታንያ የሚገኘው የሮያል ኮሌጅ የህፃናት ጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ይፋ ባደረጉት ጥናት፣ በህፃናት ምግብ ውስጥ የሚኖረው የስኳር እና ቅባት መጠን አነስተኛ ሊሆን እንደሚገባው አስታውቀዋል።

ባለሙያዎቹ ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸው በሚያቀርቡት ምግብ ውስጥ የሚኖረውን የስኳርና የቅባት መጠን ገደብ ሊያበጁለት እንደሚገባም ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም ስኳርና ቅባት የሚበዛባቸውን ምግቦች ለህፃናት መመገብ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ነው ያሉት።

በአንፃሩ ህፃናት ቅባት ከሚበዛባቸው ምግቦች ይልቅ አትክልትና ፍራፍሬ ነክ ምግቦችን ቢያዘወትሩ ለጤናቸው መልካም መሆኑንም አመላክተዋል።

በህፃናት ምግብ ውስጥ የሚኖረውን የስኳር መጠን መቀነስም፥ ህፃናት ለምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ለጥርስ መበስበስ እንዲሁም ጤናማ ላልሆነ ውፍረት የመጋለጥ እድላቸውን ለመከላከል ያስችላል ተብሏል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)