የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ አይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም እገዳ መጣሉን ገለጸ፡፡
ባለስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 በተሰጠዉ የምግብ ጥራና ደህንነት የማረጋገጥ ስራዎች መሰረት በምግብ ምርቶች ላይ መሰረታዊ የገላጭ ጽሑፍ ክፍተት ያለባቸዉና የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ መሆኑን ለዋልታ በላከዉ መግለጫ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም የንጥረ ነገር ይዘት የሌላዉ፣ የተመረቱበት ቀን ማብቂያ የሌላቸዉ እና የአማራች ድርጅቶታቸዉን የማይታወቁ የከረሜላ፣ የገበታ ጨዉ፣ ማር፣ የለዉዝ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ የሕጻናት ምግብ፣ እንዲሁም የቢምቶና አቼቶ ምርቶች ላይ እገዳ መጣሉን ታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ጆሊ ሎሊፓፕ
2. አናናስ ከረሜላ
3. ኮላስ ከረሜላ
4. ኦሊ ፓፕ
5. ቤስት ከረሜላ
6. የስ ከረሜላ (ኮፊ ከረሜላ)
7. ማሚ ኔኒፓፕ
8. ሳራ ከረሜላ
9. ጃር ሎሊፓፕ
10. ፀሀይ ሎሊፓፕ
11. ዩኒክ ሎሊፓፕ
12. እንጆሪ ከረሜላ
13. ብርቱካን ከረሜላ
14. ይናቱ ሎሊፓፕ
15. ሃለዋ ከረሜላ አምራች ድርጅት
16. አፍያ የተፈጥሮ ማር
17. ሪትም ማር
18. በላይ ማር
19. ዊዲ የገበታ ጨዉ
20. ሱላ የገበታ ጨዉ
21. ናይ የገበታ ጨዉ
22. ሃያት የገበታ ጨዉ
23. አቤት የገበታ ጨዉ
24. በእምነት የገበታ ጨዉ
25. እናት የገበታ ጨዉ
26. አባይ የገበታ ጨዉ
27. አባት የገበታ ጨዉ
28. ሴፍ አዮዳይዝ ጨዉ
29. ጣዕም የገበታ ጨዉ
30. ደስታ የለዉዝ ቅቤ
31. አስነብ የለዉዝ ቅቤ
32. ኑኑ የለዉዝ ቅቤ
33. አቢሲኒያ የኦቾሎኒ ቅቤ
34. ብስራት ለዉዝ
35. ፈሌ የለዉዝ ቅቤ
36. ሳባ
37. አዳ የለዉዝ ቅቤ
38. አደይ አበባ
39. ቀመር የኑግ ዘይት
40. ምሳሌ የህፃናት ምግብ
41. ኤልሞ የልጆች ምግብ
42. ሂሩት የህፃናት አጃ
43. ዘይነብ የህፃናት አጥሚት
44. ተወዳጅ ገንቢ የህፃናት አጥሚት
45. ተወዳጅ የህፃናት ሽሮ
46. ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህፃናት ሽሮ
47. ዴኮ ቪንቶ
48. እስፔሻል ቪንቶ
49. ዳና ቪንቶ
50. ቃና ቪንቶ
51. ላራ ቪንቶ
52. ዛግል አቼቶ
53. ናይስ አቼቶ
54. አምቴሳ አቼቶ
55. ማይ አቼቶ
56. መስ አቼቶ
57. ቫይኪንግ አቼቶ
ሕብረተሰቡ ከላይ የተዘረዘሩትን ምርቶች ሲያገኝ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላት ወይም ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነፃ ስልክ መስመር 8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ባለስልጣኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡