የጤና ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞችን የጤና ተደራሽነት የሚያጎለብቱ መተግበሪያዎችን ይፋ አደረገ

የጤና ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞችን የጤና ተደራሽነት የሚያጎለብቱ መተግበሪያዎችን ይፋ አደረገ፡፡

ከአገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ 15 በመቶ የሚሸፍኑት አካል ጉዳተኞች፣ በቤተሰብ ጤና መምሪያ ተደራሽ ለማድረግ በምስልና በድምፅ በህትመትና በስማርት ሞባይሎች የሚሰሩ መተግበሪያዎችን አዘጋጅቶ ነው ሚኒስቴሩ ይፋ ያደረገው፡፡

ይህ መተግበሪያ አዲስ አበባ በሚገኙ ሆስፒታሎች አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረ ሲሆን፣ በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ለማስፋፋትም ከኢትዮጵያ መስማት ከተሳናቸው ማህበርና ከኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማህበር ጋር በመሆን መተግበሪያውን ለማሰራጨት እየሰራ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

መተግበሪያዎቹ ዓይነ ስውራን በብሬል ማንበብ እንዲችሉ፣ መስማት ለተሳናቸው ደግሞ በድምፅ ስለ ጤና መረዳት እንዲችሉ ተብለው የተዘጋጁ ናቸው፡፡

የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን የጤና ተደራሽነት የዜጎች መብት በመሆኑ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል፡፡

በጤና ተቋማት ላይ የሚስተዋለው የተደራሽነት ችግርን ለማስተካከል ደግሞ የተለያዩ ጥናቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል፡፡ መረጃው የኢቲቪ ነው፡፡