ዶ/ር አሚር ከአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ጋር ተወያዩ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን እና የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ጋር በኮንጎ ብራዛቪል እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ 69ኛ ዓመታዊ ጉባዔ ጎን ለጎን ተወያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለማጠናከር፣ የመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ስርዓትን ለማጎልበት በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በተለይም ክትባት፣ የመረጃ አብዮት እና የዘርፈ ብዙ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ወይይት እንዳደረጉ የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር ገልጸዋል፡፡

በጉባዔው ላይ በአህጉሪቱ በጤና ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው።