የጃፓን ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ ደም መስራታቸውን አስታወቁ

የጃፓን ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ ደም መስራታቸውን አስታወቁ፡፡

በጃፓን ተመራማሪዎች ቤተ ሙከራ የተሰራው ሰው ሰራሽ ደም የትኛውም የደም አይነት ላላቸው ታማሚዎች ሊውል እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

ሰው ሰራሹ ደም ከኦክስጅን ተሸካሚ የቀይ የደም ሴሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ደም እንዲረጋ የሚያስችል ፕላቲሌትን ያዘለ መሆኑም ታውቋል፡፡

ሰው ሰራሹ ደም በ10 ከፍተኛ የደም መፍሰስ ባጋጠማቸው ጥንቸሎች ላይ ተሞክሮ የስድስቱን ህይወት ለመታደግ ተችሏዕል፡፡

ደሙ ከተፈጥሮአዊው ደም ጋር ተቀራራቢ ይዘት እንዳለውም ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡- ደይሊ ሜል)