የአንድሮይድ ስልኮች የሰዎችን የግል መረጃዎችን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ ተመለከተ

በመላው  ዓለም  በስፋት  በጥቅም ላይ የዋሉ  የአንድሮይድ ስልኮች  በሚስጥር  የሰው ልጆችን  የግል ህይወት የተመለከቱ መረጃዎችን  ያለፈቃድ  የማስተላላፍ  ክፍተት እንዳለባቸው አንድ ጥናት  ጠቆመ ።

የአንድሮይድ  ስልክ ተጠቃሚ የሆነ አንድ ግለሰብ ምንም ሳያውቅ የትቦታ እንደሚገኝ ፣ የሚያደርገውን የስልክ ልውውጡን በተመለከተና ሌሎች የግል ሚስጥሮቹን  ለማወቅ በሚያስችል ሁኔታ በሌላ ግለሰብ መረጃዎቹ  ሊበረበርበት እንደሚችል  ጥናቱ  አሳይቷል ።

በአንድሮይድ ስልክ ላይ የተጫኑ አፕሊኬሽኖች ፣ ድምጾችናሌሎች መጠቀሚያ  ሶፍትዌሮች  ሚስጥሮች አደጋ ላይ  እንዲወድቁ   ሁነታዎችን የሚፈጥሩ መሆናቸው ተገልጿል ።

ከአንድ መቶ በላይ  በሚሆኑ የጎግል አፕሊኬሽኖች ላይ በተካሄደው ጥናት እንደታወቀው የስልክ ተጠቃሚዎች አፕሊኬሽኖችን አውርደው  በሚጠቀሙበት ወቅት ከተጠቃሚው ፍቃድ ውጪ  መረጃዎችን  የመውሰድ ሁነታ ይታይባቸዋል ።

እንደ ማልዌር የመሳሰሉ  አፕሊኬሽኖች ከአንዱ ስል ወደሌላው በሚላኩበት ጊዜ  የተቀባዩን  ቁልፍ መረጃዎች በመበርበር  ለሚፈለገው ዓለማ ማዋል እንደሚቻል ጥናቱ  አመልክቷል ። 

በጎልግል ጥቅም ላይ ከወዋሉት  100ሺ የሚሆኑ ታዋቂ  አፕሊኬሽኖች ውስጥ  የጥናት ቡድኑ እንዳረጋገጠው 23ሺ 495  መረጃዎችን  መበርበር የሚያስችሉ  ጥንድ አፕሌኬሽኖች መሆናቸው  ተጠቁሟል ።

አፕሊኬሽኖቹን የተኛውም ተጠቃሚ ካወረደ በኋላ የግል መረጃ ያለምንም ፈቃድ  የግል  መረጃን  ለመበርበር ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ ።

የጥናቱ  ተንታኞች እንደሚናገሩት በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚጫኑት አፕሊኬሽኖች  እርስ በራሳቸው የሚናበቡና መረጃም የሚነግዱ መሆኑ ጥናቱ በጉልህ አሳይቷል ።