5ጂ ቴክኖሎጂ ለበሱ ፋሻ ሊመረት መሆኑ ተገለጸ

በሰው  ላይ  ቁስል ሲኖር ለመሸፈን የህክምና ባለሙያዎች የሚጠቀሙበትን ፋሻ በ5 ጂ ቴክኖሎጂ ዳብሮ ሊመረት መሆኑን  ተገለጸ ፡፡

የ5ጂ ቴክኖሎጅ  ፋሻው ጉዳት በደረሰበት የሰው አካል ላይ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ጉዳት የደረሰበትን የሰውነት ክፍል ሁኔታ በተመለከተ አጠቃላይ  ወቅታዊ መረጃዎችን ለዶክተሮች የሚልክ መሆኑ ተገልጿል ።

የ5ጂ ቴክኖሎጂ  የተገጠመለት የፋሻ ፈጠራ  ውጤት  12 ወራት ውስጥ  አገልግሎት  እንደሚውል  ተገልጿል ።

አዲስ የፈጠራ ውጤት የሆነው  5ጂ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ፋሻ  ክትትል  ስለሚደረግለት  ታካሚ  የጤና ሁኔታ ፣ የህክምና እርዳታ ያስፈልገዋል አያስፈልገውም  የሚለውን  መረጃ  ለተመደበው ዶክተር   ያስተላልፋል ።

የ5ጂ ቴክኖሎጂ ፋሻ ፈጠራን  የሚመራው   የሳዋንሲ ዩኒቨርስቲ የስነህይወት ትምህርት ክፍል ሲሆን  ቴክኖሎጂውን እውን ለማድረግም  1 ነጥብ 3 ቢሊዮን የአሜሪካ  ዶላር  እንደሚያስፈልግ  ተገልጿል ።

የትምህርት ዘርፉ ሊቀመንበር  የሆኑት ፕሮፌሰር ማርክ ክሊመንት በበኩላቸው የዚህ ቴክኖሎጂ እውን መሆን የህክምናውን ዘርፍ   አንድ አርምጃ  ወደፊት ይወስደዋል ብለዋል ።