ተስላ የሰው አንጎልን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ ለመፍጠር እየሠራ ነው

ተስላ የተባለ ኩባንያ የሰው ልጅ አንጎልን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ  የማይክሮ  መጠን ያለው  አዲስ  ቴክኖሎጂ ለመፍጠር  እየሠራ መሆኑን አስታወቀ ።

ቴክኖሎጂው ኑራሊንክ የተባለ ስያሜ ያለው ሲሆን አዕምሮን ከኮምፒውተር ሲስተም ጋር  በማገናኘት የሰው ልጅ  አዕምሮውን የማሰብ   አቅምን የሚያሳድግ መሆኑ ተገልጿል ።

በካሊፎርኒያ የሚገኘው ይህ ተስላ የተባለ ኩባንያ ኑራሊንክ የተባለው አዲስ ቴክኖሎጂን ለገበያ ለማቅረብ እየሠራ ሲሆን ቴክኖሎጂው የሰው አዕምሮን የሚጎዱ ስትሮክና ካንሰር የመሳሰሉት በሽታዎችን ለመከላከል ሊያግዝ የሚችል ነው ተብሎለታል፡፡   

ቴክኖሎጂው የሰዎች ጭንቅላት ውስጥ ብዙ የተከማቹ ሃሳቦችን  በአንድ ላይ  ለማመን በሚከብድ ሁኔታ በመጭመቅ ለንግግር ወይም ለጽሁፍ እንዲመች የማድረግ ሥራን እንደሚያከናውን  የተሰላ ኩባንያ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ ቴክኖሎጂ  ምንም የአካል እና የአይምሮ ጉዳት የሌለባቸው ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለማድረግ ምናልባት ከ 8-10 አመት ሊፈጅ  እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በወርሃ መጋቢት  ዎል ስትሪት ጆርናል የተባለ ድረ ገፅ  የሰው አንጎል ከኮምፒውተሮች ጋር የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ  የሚያመርት   ኩባንያ ስራውን ጀምሯል ሲል ዘግቦ ነበር ፡፡ (ምንጭ : ሮይተርስ )