ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ወደ ግማሽ የሚጠጋዉ የእንግሊዝ ኢኮኖሚ ላለፉት አስራ ሁለት ወራቶች በሳይበር ጥቃት ሲቃወስ ቆይቷል፡፡
ከ46 በላይ የሚሆኑት የእንግሊዝ ካምፓኒዎች እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ ባለፉት አመታት ቢያንስ በአንድ የደህንነት መስኮት በደረሰዉ የሳይበር ጥቃት በአማካኝ ከ1ሺ570 የእንግሊዝ ፓዉንድ ኪሳራ ደርሷል፡፡
67 በመቶ መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የቢዝነስ ኩባንያዎች እና 68 በመቶ በላይ የሚሆኑት ትላልቅ የቢዝነስ ኩባንያዎችን ጨምሮ በደረሰባቸዉ የሳይበር ጥቃት ከ20ሺ በላይ ፓዉንድ ያላነሰ ኪሳራ በየዓመቱ ይደርስባቸዋል፡፡
የሃሰት ኢሜሎችን በመጠቀም የሰዎችን የሚስጥር ኮድ እና አስፈላጊ መረጃዎችን መዉሰድ የሳይበር ጥቃት ከሚያደርሳቸው ጉዳቶች መካከል የተለመዱት ናቸው ፡፡
የሳይበር ደህንነት ጥቃት ጥናት እንደሚያመለክተዉ እነዚህ ጥቃቶች የሚያስከትሉት ጉዳቶች በገንዘብ ብቻ ሳይሆን መረጃ ማጥፋት የኔትዎርክ አገልግሎትን ማቋረጥ ጨምሮ እንደሆነና ይህ ደግሞ በኩባንያዎቹ ላይ ቀላል የማይባል ኪሳራ ይዳርጋሉ፡፡
አብዛኞቹ የቢዝነስ ተቋማት እራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል ተግባር ቅድሚያ የሚሠጡ ሲሆን የሳይበር ጥቃት ደህንነትን ለማስጠበቅ በሶስት ክፍል ተከፍለዉ ቁጥጥር ያደርጋሉ ፡፡
መሰረታዊ የሳይበር ጥቃት መቆጣጠር መብትን በመጠቀም በየደረጃዉ የሚገኙ የቢዝነስ ተቋማት ከሳይበር ጥቃት እራሳቸውንና ተቋሞቻቸውን ለመካላከል እንደሚቻልና እና የአሠራር አቅሙንም ማሳደግ እንደሚገባ የናሽናል ሳይበር ሴኩሪቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሲርያን ማርቲን ተናግረዋል፡፡