ደቡብ አፍሪካ በዓለም ትልቁን ራዲዬ ቴሌስኮፕ ገነባች

የዓለም ትልቁን ራዲዩ ቴሌስኮፕ በደቡብ አፍሪካ መገንባቱ ተገለጸ ፡፡

ቴሌስኮፑ እኤአ በ2030 ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ራዲዩ ቴሌስኮፑ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን እና አውስትራሊያን በቅርብ ርቀት ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሏል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ተግባራዊ የተደረገው  የአለማችን ትልቁ  ራዲዩ  ቴሌስኮፕ በሀገሪቱ ምክትል ፕሬዘዳንት ዴፊድ ማቡዛ  ሓሳብ አመኝጪነት ለሙከራ የበቃ ሲሆን እኚህ ሰው በተለይም ለመጀመሪያዎቹ ሥራዎች ትልቅ ሚና እንደነበራቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

ራዲዩ ቴሌስኮፑ እኤአ በ2030 ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ የሚገባ ሲሆን 3ሺህ ሳህኖችን በስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ይሆናል፡፡

ይህም ለበርካታ አፍሪካ ሀገራት እና ለአውስትራሊያ የራሱ የሆነ ጥቅምን በመሥጠት ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ይዉላል ተብሏል፡፡

ራዲዩ ቴሌስኮፑ እስከዛሬ በአለማችን ከነበሩ ቴሌስኮፖች በ50 እጥፍ አቅም ያለው እና ከ10 ሺህ እጥፍ ፈጣን ነው ተብሏል፡፡

ቴሌስኮፑ ያለውን አቅም እና ፍጥነት በመጠቀም በሰማይ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ነገሮችን አጥርቶ በማሳየት በተለይም በከባቢ አየር ላይ የሚገኙ አካላትን በአንድ ስኩዬር ኪሎሜትር ውስጥ ጥርት አድርጎ በማሳየት ለተመራማሪዎች በዚህ ዙሪያ ለሚሠሩ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ያግዛል ተብሎለታል፡፡

የዚህ ፕሮጀክት ተመራማሪ የሆኑት ፈርናንዶ ካሚሎ እንደተናገሩት ከሆነ ራዲዩ ቴስኮፑ የዓለማችን ምርጡ እና ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡

ከዚህም በላይ ምስሎችን መሃል ለመሃል አድርጎ ማሳየት የሚችል በመሆኑ በአንድ አመት ውስጥ ከሚሊኪ ዌይ ጋላክሲ 30 ሺህ ብርሃን በመጠቀም ማንኛውንም ምስል በጣም ጥርት ባለ ሁኔታ  ከመሬት ላይ በማንሳት ትክክለኛ ነገር ያስቀምጣል ብለዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የተሠራው ቴሌስኮፕ የተለያዩ አለም አቀፍ ሀገራት በትብብር እንዲሰሩ ያስችላል የተባለ ሲሆን ይህንን ለመጠቀምም አውስትራሊያ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ህንድ ጣሊያን፣ ኒውዝላንድ ፣ስውዲንና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ፍላጎት ማሳየታቸውን የሲጂቲኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡     

ከዚህም ባለፈ  ከተለያዩ በሳህኑ ላይ በተገጠሙ ኤሌክትሮኒክስን በመጠቀም የደንበኞችን ፈጣን የመረጃ ስርዓት ለመቆጣጠር ስርዓት ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርአት ለማቋቋም እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡ (ምንጭ: ሲጂቲኤን)