ቻይና በሰዓት 1,500 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል ባቡር እየገነባች ነው

ቻይናዊያን ሳይንቲስቶች በአለማችን በሰዓት 1500 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል ፈጣን ባቡር እውን ሊያደረጉ ነው፡፡

በደቡብ ምራብ ቻይና ጃዮቶን ዩኒቨርሲቲ ፈጣኑን ባቡር እውን ለማድረግ ጥናት ያደረጉት ዣንግ ዌሁ እና አጋሮቹ ቻይና ከእለት ወደ እለት እየፈተናት የመጣውን የህዝብና የጭነት ማጓጓዣ ችግር ለመቅረፍ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡

ቴክሎሎጂው በፈረንጆቹ 2021 እውን ይሆናል ተብሏል፡፡

በ2013 ኤሎን ሙሳክ የተባለው የሀገሪቱ ሳይንቲስት ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጣን ባቡር ውድድር ፅንስ ሀሳብ ማፍለቁን ተከትሎ በርካታ ቻይናውያን ዜጎች ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ዣንግ እና የቡድን አጋሮቹ የውድድሩን አላማ እውን በማድረግ ቀዳሚ ሆነዋል እየተባለ ነው፡፡

ኮሶስት አመታት ባነስ ጊዜ ውስጥም የባቡሩን መስመር መዘርጋት ስራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት አንደሚጀምር እና ባቡሩንም ለአለም ተደራሽ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

መጪው ዘመን በፈጣን ባቡር፣ በኒዩክለር ሀይል ግንባታ፣ በዘመናዊ ወታደራዊ አቅም አንዲሁም በአየር ትራንሰፖርት ረገድ የሚደረግ የቴክኖሎጂ ውድድር ዘመን አንደሚሆን ሲጂቲኤን በዘገባው አመላክቷል፡፡