ደቡብ አፍሪካ የትምህርት ስርአቷን ለማሻሻል የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ለመተግበር እየሰራች ነው

ደቡብ አፍሪካ የትምህርት ስርዓቷን ለማሻሻል የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ለመተግበር እየሰራች እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በሀገሪቷ ቀደም ባሉት አመታት ባህላዊ የመማር ማስተማር ስትራቴጂዎችንና ልምዶችን ሲጠቀም የነበረዉ የትምህርት ዘርፍ በርካታ ችግሮች ሲገጥሙት መቆየቱ ይነገራል፡፡

በሚያጋጥማቸዉ የመማሪያ ቁሳቁስና እና የግብአት እጥረት በርካታ ደቡብ አፍሪካዊያን ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ለማቋረጥ ሲገደዱ ቆይተዋል፡፡

አሁን ላይ ግን ሀገሪቱ በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመቀነስና የሃገሪቱን ስርአተ ትምህርት አሰጣጥ ለማሻሻል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በዘርፉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ገልጻለች፡፡

ጂና ቤስተር በደቡብ አፍሪካ በተዘጋጀዉ ኢዱክ የተሰኘዉ ኤግዚቢሽን አስተባባሪ ሲትሆን የደቡብ አፍሪካ የትምህርት ስርአትን ለማሻሻል ቴክኖሎጂ በትምህርት ቤቶች እንዲተገበርና የመምህራኑንም ክህሎት በዛዉ ልክ ለማሳደግ አላማ ያደረገ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በኤግዚቢሽኑ የቀረቡት የቴክኖሎጂ ዉጤቶችም የተማሪዎችን የሂሳብ እና የምርምር አቅም ከፍ የሚያደርጉ አጋዥ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ ተማሪዎች እየተዝናኑ እንዲማሩ ከማድረጉም በተጨማሪ የማሰብና የመመራመር ክህሎትን እንዲያዳብሩ ያስችላሉ ነው የተባለው፡፡

ማይንድክራፍት የተሰኘዉ የጌም አይነት በዚህ ቴክኖሎጂ ዉስጥ የተካተተ ሲሆን ይህም የተለያዩ እርካቦችን በመደርደር ተማሪዎቹ እየተዝናኑ ወደ ተለያዩ ደረጃዎች ለማለፍ በሚያደርጉት ጥረት እግረመንገዳቸዉንም ደግሞ የመመራመርና አዳዲስ ግኝቶችን የማምጣት ክህሎታቸዉን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል፡፡

ካሂል ራምጄ በደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሲሆን እሱም ቴክኖሎጂዉ በክፍል ዉስጥ እንዲተገበር መደረጉ እንዳስደሰተዉና ተጨማሪ ክህሎት እንዲያዳብር እንደሚረዳዉ ገልጸዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በተለይም በአፍሪካ ያለዉ የትምህርት ስርአት የየሃገራቱን ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ  በመሆኑ አህጉሪቱ በትምህርት መጠቀም የነበረባትን ሁሉ እንዳትጠቀም አድርጓት መቆየቱ ተገልጸዋል፡፡

አሁን ደቡብ አፍሪካ በቴክኖሎጂ የትምህርት ስርአቷን ለማሻሻል እያደረገች ያለችዉ ጥረት አጠናራ እንደምትቀጥልም በዘገባዉ ተጠቅሷል፡፡ (ምንጭ፤ ሲጂቲኤን)