የናሳ ተመራማሪዎች ለህይወት ተስማሚ የሆነች አዲስ ፕላኔት ማግኘታቸውን አስታወቁ

የናሳ ተመራማሪዎች ‘ሱፐር ኧርዝ’ ሲሉ የሰየሟትን አዲስ ፕላኔት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመጠኗ የመሬትን እጥፍ ታክላለች የተባለችው አዲሷ ፕላኔት ከከዋክብቷ አንፃር ለህይወት ተስማሚ በሆነ ርቀት ውስጥ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡

ይህም በፕላኔቷ ላይ ህይወት ሊኖር ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል ነው የተባለው፡፡

ፕላኔቷ አለታማ አሊያም እንደኔፕቲዩን በጋዝ የበለፀገች ልትሆን እንደምትችል የናሳ ተመራማሪዎች የገለጹ ሲሆን ፕላኔቷ ያልተለመደችና ከቀድሞ ፕላኔቶች ልዩ እንደሆነች በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ (ምንጭ፡- ዴይሊ ሜል)