አንድ ወጣት ከወዳደቁ ቁሳቁሶች በውሃ ላይ የሚነዳ የብስክሌት ጀልባ መስራቱ ተገለጸ

አንድ ወጣት ተማሪ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች በውሃ ላይ የሚነዳ የብስክሌት ጀልባ (Pedal-Boat) መስራቱ ተገለጸ፡፡

ጌታባለው መኩሪያው የተባለው ወጣት በባህርዳር ዩኒቨርስቲ 3ኛ ዓመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወጣቱ የወዳደቁ ፒፒሲ ትቦዎች፣ የላሜራ ብረቶችና ፌሮዎች እንዲሁም አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የብስክሌት አካላትን ተጠቅሞ ነው የብስክሌት ጀልባ (Pedal-Boat) መስራት የቻለው፡፡

ጌታባለው መኩሪያው ከወዳደቁ ቁሳቁሶች የሰራውን የብስክሌት ጀልባ (Pedal-Boat) በውሃ ላይ በመንዳት ሙከራ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

(ምንጭ፡-የጃዊ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት)