ኢትዮጵያ በመጪዉ ህዳር ወር ሳተላይት እንደምታመጥቅ ተገለፀ

ኢትዮጵያ በመጪው ህዳር ወር ሳተላይት እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ ለዋልታ ተናገሩ፡፡ 

የበላይ ጠባቂው እንዳሉት ሳተላይቱ ከመጠቀ በኋላ በተለይም በግብርና እና በመረጃ ልውውጥ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

ሳትላይቶችን ወደ ህዋ ያመጠቁ ሃገራት ከዘርፉ በሚያገኙት ገቢ ምጣኔ ሃብታቸው ማደጉን የገለፁት አቶ ተፈራ ኢትዮጵያም ሳተላይቷን ካመጠቀች ለሳትላይት አገልግሎት የምታወጣውን ወጪ እንደሚያስቀርላት አክለዉ አብራርተዋል፡፡

የመጀመሪያው ሳተላይት የሚመጥቀው በቻይና ሲሆን በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ደግሞ የሳተላይት ሙሉ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ ይከናወና ብለዋል፡፡

ተቋሙ በዚሁ ዘርፈ ላይ የሚያገለግሉ መሃንዲሶችንና ሳይንቲስቶችን ማብቃቱን ገልፀዋል፡፡