የኢኖቬሽን ማዕከሉ ግንባታ ከ50 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቡራዩ ከተማ ላይ እያስገነባው ያለው የኢኖቬሽን ማዕከል ግንባታ ከ50 ከመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ 

ማዕከሉ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች እንዲማሩበት ታስቦ እየተገነባ ያለ ቢሆንም አሁን ግን ልዩ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ማዕከሉ ገብተው የፈጠራ ስራዎቻቸውን አዳብረው ወደ ምርት ቀይረው እንዲወጡ የሚያስችል ተደርጎ ያደገ ነው ተብሏል፡፡

የግንባታ ሂደቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰው ሃብት ቴክኖሎጂና መገናኛ ቋሚ ኮሚቴዎች ተጎብኝቷል፡፡

ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ ከተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ የዘገየ ሲሆን በአካባቢው ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ ትውልድ ተሻጋሪ የሆነው ይህ ማዕከል ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡ (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)