የቱሪዝም ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ሥራ ላይ ሊውል ነው

“ቱሪዝም ሳተላይት አካውንት” የተባለን የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በኢትዮጵያ ስራ ላይ ለማዋል ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኑን ቱሪዝም ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወይዘሪት ሌንሳ መኮንን እንደገለጹት ይህ መተግበሪያ በቱሪዝሙ ዘርፍ የአገልግሎት ሰጭና ተቀባዩን ሙሉ መረጃ ተደራሽ የሚያደርግ ነው፡፡

የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ያለው ድርሻ ጉልህ በመሆኑ ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን በቴክኖሎጂ ተደግፎ መስራት ጥሩ አማራጭ እንደሆነም ወይዘሪት ሌንሳ ገልጸዋል፡፡

ቱሪዝም ሳተላይት አካውንትን አንዳንድ የአለም ቱሪዝም አባል አገራት ተግባራዊ ያደረጉት ሲሆን መተግበሪያው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተደግፎ ወደ አገራቱ የሚገቡ ቱሪስቶችን የሚመለከት ሙሉ መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡

ደቡብ አፍሪካና ሞሪሽየስ ይህን መተግበሪያ እየተጠቀሙ እንደሆነ ታውቋል፡፡