በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቀናጀ ዘመናዊ ግብርና በክልሎች ሊተገበር ነው

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቀናጀ ዘመናዊ ግብርና በተለያዩ ክልሎች ሊተገበር መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡  
ሚኒስቴሩ ከኦሮምያ ክልል መንግስትና ከመቱ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የተቀናጀ ግብርና ስራ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
የተሻለ ምርት የሚሰጡ እንስሳት፣ ለእንስሳቱ የሚሆን መኖ፣ የእንስሳቱ የጤና እንክብካቤ እና የገበያ ትስስር ተቀናጅተው በሚተገበሩበት ሁኔታ የምክክሩ ትኩረት ነበር።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂ፣ የኦሮምያ ክልል ቦታ፣ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከጤና ጋር የተያያዙ ስራዎችን አቀናጅተው ይሰራሉ።
ኦሮምያ ክልል መቱ፣ ወለጋ፣ ጅማ፣ አምቦ እንዲሁም ቤንሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች ስራው የሚሰራባቸው አካባቢዎች ናቸው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር ግብርናው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆንና ማህበረሰቡ ከግብርናው የሚገባውን እንዲጠቀም ሚኒስቴሩ መስሪያ ቤቱ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። 
ፕሮጀክቱ በትግራይ ክልል ተሞክሮ ውጤታማ የሆነ ፕሮጀክት ነው። 
በቀጣይም በሁሉም ክልሎች የማስፋፋት እቅድ ተይዟል።