የኪሎግራም ልኬት ተለወጠ

ለ130 ዓመታት ገደማ የኪሎግራምን ክብደት ይወስን የነበረው ልኬት (Standard) ተቀይሯል፡፡

በፓሪስ አቅራቢያ በሚገኘ ስፍራ የተቀመጠው የኪሎግራም ልኬት ሆኖ ያገለገለው የብረት ሲሊንደር ከስራው በጡረታ ሊሰናበት ግድ ሆኗል፡፡

በምትኩም ፕላንክ ኮንስታንት በመባል በሚታወቀው የኳንተም ብዛት ተተክቷል፡፡

ይህ ልኬት ታድያ በህዋም ሆነ በጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ አይለወጤ ልኬት እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡

ለንፅፅር ትንሽ ጭረት እንኳን ቢያጋጥመው የመጠን ለውጥ በማምጣት ልኬቶችን ሊያዛባ ከሚችለው የብረት ሲሊንደር አኳያ ይህ መለኪያ በላቀ አስተማማኝ ነው፡፡

ይህን የልኬት ለውጥ ባፀደቀው 26ኛው የክብደትና ልኬቶች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተጨማሪነት የሙቀት፣ ኤሌክሪክ ከረንትና የቁሶችን መጠን መለኪያ የሆኑት ኬልቪን፣ አምፒር እና ሞል ድግም ልኬታቸው ተወስኗል፡፡

ሆኖም ይህ ማለት ቀኑ ያጥራል ወይም ክብደት ይጨምረል ማለት አይደለም፡፡

በክብደትም ሆነ ጊዜ ላይ የሚደረጉት የልኬት ለውጦች ከተለመደው የኪሎግራም አሊያም ሴኮንድ መጠን ልዩነት እንዳያመጡ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚከውኑ ይሆናል መረጃው የሳይንስ ኒውንስ ነዉ፡፡