ኢትዮጵያና ቻይና የኮሙኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ቻይና የኮሙኒኬሽንና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ፍሬምወርክ ስምምነት አደረጉ። 
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ሰለሞን በላይ (ዶ/ር) እና የቻይና ሮኬት ካምፓኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ቺንፒንግ ፈርመውታል። 
ግንባታው በኢትዮጵያና ቻይና ባለሙያዎች ትብብር የሚከናወን ሲሆን 50 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴት እንዲጠቀም ይደረጋል። 
በግንባታው የሚሳተፉ ኢትዮጵታውያን ከቻይና የቴክኖሎጂ ልምዱን ይወስዳሉ ተብሏል። ተጠቃሚ መለየት፣ ማስተባበር፣ ፍላጎትና ቦታ መረጣ የመሳሰሉት ተግባራት ሰኔ ወር ላይ ይጀመራሉ። 
የአሁኑ የሳተላይት ግንባታ ፍሬምወርክ ስምምነት ሳተላይትን የስራ እድል መፍጠሪያ እና ሃብት ማመንጫ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው። 
በሁለቱ ሀገራት ትብብር የተሰራችው የመጀመሪያዋ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ህዳር 2012 ወደ ህዋ እንደምትላክም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡