ኢትዮጵያ የአለምአቀፉን የቴሌኮም ልማት ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመረጠች

የአለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት (ITU) ኢትዮጵያን እኤአ በ2021 የሚካሄደውን የአለምአቀፍ ቴሌኮም ልማት ጉባኤ (WTDC-21) እንድታስተናግድ በሙለ ድምፅ መረጠ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያ መመረጧን ተከትሎ ለሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጉባኤው በየ4 አመቱ የሚካሄድ ጉባኤ ሲሆን ከተጀመረ ባሳለፈው 25 አመታት ውስጥ በአፍሪካ ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆንም ታውቋል።

በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የቴሌኮሙዩኬሽን ህብረት ምክር ቤት ስብሰባ ኢትዮጵያ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተነግሯል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ይህን አለም አቀፍ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ልማት ኮንፈረንስ በፈረንጆቹ 2021 እንደምታዘጋጅ ነው የተነገረው፡፡

አለም አቀፉ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ልማት ኮንፈረንስ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን እኤአ 1994 ጀምሮ በአፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው ይሆናል መረጃዉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ነዉ፡፡