የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲደግፋቸው የነበሩ 9 ምርምሮችን አስመረቀ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ጀማል በከር የምርምር ስራዎቹ ወደ ስራ ገብተው የስራ እድል እንዲፈጥሩ እና የማህበረሰቡን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ ለማድግ መስሪ ቤቱ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ምርምሮቹ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄዱ የነበሩ ሲሆን ተጠናቅቀው ወደ ምርትና አገልግሎት መግባት የሚችሉ መሆናቸው የተረጋገጡ ናቸው፡፡

ችግር ፈቺ፣ ዘርፍ ተሸጋሪ እና ወደ ስራ ሲገቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ናቸውም ተብሏል፡፡

ከፋብሪካ በሚወጣ ዝቃጭ የተበከሉ ወንዞችን ማከም፣ የተቀናጀ የውሃ ሃብትና ግብርና፣ ኩቺኒያ የሚባል ተባይን የሚያጠፋ መድሃኒት፤ የበቆሎ ባክቴሪያ ማጥፊያ መድሃኒት እና ሌሎችም የተመረቁ ምርምሮች ናቸው፡፡