በባህር ውስጥ አዞን ጨምሮ 16 የባህር ውስጥ እንስሳት እንዳሉ ለዋናተኞች የሚጠቁም ድሮን ተፈጠረ

በባህር ውስጥ አዞን ጨምሮ 16 የባህር ውስጥ እንስሳት በአቅራቢያቸው ስለመኖራቸውለዋናተኞች የሚጠቁም ድሮን መፈጠሩ ተሰምቷል።

'ሊትል ባይ ሊትል ሪፐር ግሩፕ' የተባለ የአውስትራሊያ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፤ አዞን ጨምሮ 16 የባህር ውስጥ እንስሳትን ለዋናተኞች የሚጠቁም ድሮን (አነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላን) አስተዋውቋል።

93 በመቶ አስተማማኝ ነው የተባልው ድሮኑ፤ በዋናተኞች ቅርብ ርቀት የባህር እንስሳት እንደሚገኙ በድምፅ ይጠቁማል፤ የአደጋ ጊዜ መንሳፈፊያም ያቀብላል።

ሊቨርፑል ጆን ሞረስ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት ዶ/ር ሰርጌ ዊች ድሮኑን "ድንቅ ሀሳብ" ሲሉ አሞካሽተውታል።

መምህሩ፤ ድሮን ለመልካም ነገር በመዋሉ የተሰማቸውን ደስታ ሳይገልጹም አላለፉም። "ድሮን የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ መዋሉ በጎ ነገር ነው" ብለዋል።

የድሮኑን አምራች ድርጅት ከመሰረቱት አንዱ የሆነው ፖል ስከሊ-ፓወር እንዳለው፤ አዞዎች በደፈረሰ ውሃ ውስጥ በመሽሎክሎክ ከዕይታ ለመሰወር ቢሞክሩም ድሮኑ በቀላሉ ይይዛቸዋል።

(ምንጭ፦ ቢቢሲ)