ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው 

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ የሚመራ የልዑካን ቡድን በጀርመን እየተካሄደ ባለው 63ተኛው የአለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አመታዊ ስብሰባ ላይ ሀገራችንን ወክሎ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

የልዑክ ቡድኑ በቆይታው ሀገራችን በዘርፉ ያላትን ወቅታዊ ሁኔታና አቋም የሚያመላክት ንግግር አንደሚያረግ ይጠበቃል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከወቅቱ የአለም አቀፉ አቶሚክ ሀይል ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር  ኮርኔል ፌሩታ ጋር ምክክር ያደርጋሉ፡፡

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ ለማዋል የተፈራረመቻቸውን ስምምነት ለማጠናከር የወጣውን ተጨማሪ ፕሮቶኮሎች እንደሚፈርሙም ይጠበቃል፡፡