የጃዋር ርኩስ መንፈስ 

  
የኢሬቻን በአል ከልጅነቴ ጀምሬ ነው የማውቀው። ታዲያ ድሮ እንዲህ እንደአሁኑ ሳይሆን በየአጥቢያው በሚገኝ ወንዝ ላይ ውሃ የሚከማችበት ስፍራ ጋርባ (garba) ላይ ነበር የሚከናወነው። ታዲያ በዚህ ኢሬቻ በሚከናወንበት ጋርባ ላይ የአጥቢያው ሰው አንድም ሳይቀር ነበር የሚሰባሰበው፤ ከህጻን እስከአዛውንት። እንኳን ሰው እንስሳቱም ኢሬቻ ላይ ይሰበሰቡ ነበር፤ ከእረኞች ጋር። የኢሬቻ ታዳሚዎች ከዘመን ወደዘመን ያሸጋገራቸውን ፈጣሪያቸውን አመስግነው፣ መጪው መልካም እንዲሆን በአዛውንትና በመንፈሳዊ አባቶች ምርቃት ይቀበላሉ። በተለይ ህጻናት ለመለሙ የቢራ መስክ ላይ ይፈነድቃሉ። በዚህ ምክንያት ኢሬቻ  ከኦሮሞዎች አእምሮ ውስጥ የማይፋቅ አብሮ የሚኖር ትዝታ ያለው ሁነት ነው።
የኦሮሞ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ በህገመንግስት በተረጋገጠባቸው ያለፉ ሃያ አምስት ዓመታት ይህ ከኦሮሞዎች አእምሮ የማይፋቀው ኢሬቻ በኦሮሚያ አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ተደርጓል። ኢሬቻ ብቻ ሳይሆን ጥንታዊ የኦሮሞዎች የገዳ አስተዳደር ስርአትም የታላቅነቱን ያህል ክብር ተሰጥቶት እንዲተዋወቅ፣ ከዚህም አልፎ እንዲያንሰራራ ተደርጓል። አሁን በመላው ኦሮሚያ የገዳ ስርአት ተዘርግቷል። የገዳን ስርአት ምንነት ኦሮሞዎች ብቻ ሳይሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አውቆታል። ይህ ብቻ አይደለም፤ ገዳን በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (The United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization  _UNESCO) ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ማድረግ ከተጀመረ ከአስር ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። በመጪው ህዳር ወር ውሳኔ ያገኛል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ኦሮሞዎች ከአእምሯቸው የማይጠፋው የኢሬቻ በአል ትዝታቸው በትልቁ በኦሮሚያ አቀፍ ደረጃ መከበሩ ልዩ የመታደስ ስሜት ፈጥሮባቸዋል። በየአመቱ ኢሬቻን ለማክበር በሚሊየን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ወደቢሾፍቱ አርሰዲ ሃይቅ የሚሄዱት ለዚህ ነው። አኦሮሞዎች የተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው፤ ሙስሊም፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፣ ፕሮቴስታንት ክርስቲያን፣ ዋቄፈታ . . . ተከታዮች ናቸው። የተለያየ የፖለቲካ አመለካከትና አቋም ነው ያላቸው። ይሁን እንጂ ለምሉእ በኩለሄ ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበትን የኢሬቻ በአል ግን በሚያመሳስላቸው የኦሮሞ ማንነታቸው ትከሻ ለትከሻ ገጥመው mareewoo (በዓመቱ ዞረን መጣን) እያሉ፣ ወጣቶቹም በአንድ ጀማ እየጨፈሩ ያከብራሉ፣ የልጅነት ትዝታቸውን ያስታምማሉ፣ ይዝናናሉ። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኦሮሚያ ዓቀፍ ደረጃ በቢሾፍቱ አርሰዲ ሃይቅ ላይ የተከበሩት የኢሬቻ በዓላት በዚህ ስሜት በፍፁም ሰላም ነበር ሲከበሩ የቆዩት። ስለኢሬቻ በዓል የተሳሰተ ግንዛቤ የነበራቸው ኢትዮጵያውያን ከዓመት ወደዓመት ግንዛቤያቸው እይተስተካከለ ከኦሮሞ ወንድሞቻቻው ጋር በበአሉ ላይ ለመታደም መብቃታቸውም ይታወቃል። የኢሬቻን በአል ለማክበር ወደቢሾፍቱ የሚጓዘው ሰው ቁጥርም ከዓመት ወደዓመት እየጨመረ መጥቷል። ከኢትዮጵያውያን አልፎ የውጭ ሃገር ጎብኚዎችም የሚታደሙበት በዓል ለመሆን በቅቷል። እናም ኢሬቻ ከመንፈሳዊና ባህላዊ እሴትነቱ ባሻገር የቱሪዝም መስህብ በመሆን በተለይ ለቢሾፍቱና አካከባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ሁነት ለመሆንም በቅቷል።
ታዲያ ይህ በዚህ መንፈስ ሲከበር የቆየ ኢሬቻ ዘንድሮ ርኩስ መነፈስ በላው። በእነጃዋር በኩል የመጣ የግብጽ ርኩስ መነፈሰ። ኦሮሞዎች ለምሉዕ በኩለሄ ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት፣ የልጅነት ትዝታቸውን የሚያስታምሙበት፣ ወጣቶች የሚዝናኑበት፣ ጉብሎችና ኮረዶች ደምቀው ወጥተው የሚተዋወቁበት፣ የቢሾፍቱና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ከአካባቢው በብዙ እጥፍ የሚበልጠውን የኢሬቻ እንግዳ ተቀብለው በማስተናገድ የሚጠቀሙበት መሆን አልቻለም። ገና የበአሉ ስነስርአት ሳያልቅ በሁከት ታመሰ።  እንደተለመደው የፌስ ቡክ አዝማቹ ጃዋርና ሌሎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልእኮ የተረከቡ ቅጥረኞች ናቸው የዘንድሮውን ኢሬቻ በርኩስ መንፈስ የበጠበጡት።
ሰሞኑን በተለያየ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲደረግ እንደቆየው እነጃዋር የተሸከሙትን ርኩስ መንፈስ አደገኛነት ያልተረዱ ለጋ ወጣቶችን ሰሜት በሞኮርኮር  አደራጅተው የኢሬቻን በአል እንዲያውኩ አሰማሯቸው። የኢሬቻ በአል ስነስርአት ላይ የተመለከትነው ተቃውሞና ተቋወሞው የቀሰቀሰው ሁከት በድንገት የፈነዳ አልነበረም፤ የተደራጀ ነው። ጠንሳሽ፣ መሪና ፈጻሚ ያለው፤ ባጀት የተመደበለት፤ በተቻለ መጠን ከፍተኛ እልቂት ሊያስከትል በሚችል አኳኋን እንዲከወን የተቀናጀ ነው።ይህን ያደረጉት ደገሞ እነጃዋር ናቸው።
ከዶላር ጋር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገንባት የውስጥ እግር እሳት የሆነባትን ኢትዮጵያን በክፉ አይን የሚያይ የግብጽን ርኩስ መንፈስ የተረከቡት እነጃዋር ለኦሮሞ ህዝብ፣ ለባህሉና ወጉ ክብር የላቸውም። እነጃዋር የዋህ የኦሮሞ ወጣቶችን መጠቀሚያ በማድረግ የግብጣውያንን ሃገሪቱን የማተራመስና  ህዝቧ እርስ በርስ የሚባላ፣ የተከፋፈለ ደካማ ኢትዮጵያ የማየት ህልም ማሳካትን ብቻ መድረሻ ያደረጉ ክፉ አውሬዎች ናቸው። ኦሮሞዎች በሙሉ የሚያከብሩትን ታላቁን የኢሬቻ በአል ለራሳቸው ዓላማ መሳካት ለማደፍረስ መወሰናቸው፣ የተከበሩ አዛውንት አባገዳዎችን ክብር ነፍገው ማይክራፎን በመንጠቅና ትረጋጉ የሚል ጥያቄያቸውን በንቀት ችላ ማለታቸው ለዚህ አስረጂነት ሊጠቀስ ይችላል።  የክልሉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የኦሮሞ ተቃዋሚ ሃይለች የሚያከብሩትንና ጥልቅና ታሪካዊ መልዕክት ያለውን የኦሮሚያ ሰንደቃላማ በማውረድ ለማቃጠል የተደረገው ሙከራም የሁከቱ ጠንሳሾች ለኦሮሞ ህዝብና ታሪክ ምንም ደንታ የሌላቸው መሆኑን ያሳያል። የኦሮሚያን ሰንደቃላማ የማዋረድ ተግባር ከዚያ ቀደም በኦሮሚያ ውስጥ በተካሄዱ በርካታ ተቃውሞዎች ላይ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ ነው። 
በዘንድሮው የኢሬቻ በአል ላይ የተፈጸመ የእነጃዋርን ቀጣሪዎች ያስፈነደቀ ኦሮሞዎችን የመናቅና የማዋርድ ድርጊት እጅግ አሳዛኝ ነው። በሰነስርአቱ ላይ በእነጃዋር ቅስቀሳ ተደናግረው ሁከት የቀሰቀሱት ወጣቶች ድርጊት የጸጥታ ሃይሎች መንግስትን ለማሳጣት የሚመች እርምጃ እንዲወስዱ ተዕግስታቸውን የሚፈታተን ነበር። የኦሮሞ ወጣቶች የእነጃዋር ላይ ባረፈው የኢትዮጵያ ጠላቶች ርኩስ መንፈስ እየተመሩ የራሳቸውን ማንነት እንዲያዋርዱ ተደርጓል። ወጣቶቹ ያሳዩት የኦሮሞን ባህልና ወግ የሚያዋርድ ድርጊት በማንነታቸው የነበራቸው ኩራት (sabboonummaa) መሸርሸር መጀመሩን ስለሚያሳይ አስደንጋጭ ነው። ኦሮሞዎች እንኳን አሁን ማንነታቸው በተከበረበት ዘመን፣ በማንነታቸው እንዲዋረዱ ሲደረግ በነበረበት ያለፉ ስርአቶችም ቢሆን ብሄራዊ ኩራታቸው (sabboonuummaa) አልጠፋም። አሁን ግን በቅጥረኛው ጃዋርና ለኦሮሞዎች ማንነት ክብር በሌላቸው ትምክህተኞች እየተመሩ  ኦሮሞነትን የሚያዋርዱ ወጣቶችን ተመለከትን። እርግጥ እነዚህ የእነጃዋር ርኩስ መንፈስ የሚገፋፋቸው ወጣቶች ጥቂቶች ናቸው። በቅርቡ የሚገፋፋቸውን ርኩስ መንፈስ አራግፈው እንደሚጥሉም ተስፋ እናደርጋለን ።
የዋሆቹ መጠቀሚያ የሆኑት ወጣቶች የጸጥታ አስከባሪዎችን ትእግስት ለመፈታተን ከአባ ገዳዎች ላይ ማይክራፎን በመንጠቅና የኦሮሚያን ሰንደቅዓላማ አውርዶ በማቃጠል ድርጊት አልተገደቡም። የበአሉ ታዳሚዎች ሰላማዊ ሁኔታ መኖሩ እንዲሰማቸው መሳሪያ ሳይታጠቅ፣ በትር እንኳን ሳይዝ የተሰማራው የጸጥታ አስከባሪ ሃይልና በአሉን ለማከበር የታደመው ሰላማዊ ህዝብ  ላይ የድንጋይ ኡሩምታ አዘነቡ። ይሄኔ ሰዉ በድንገት ከተፈጠረው ሁከት ለማምለጥ በየአቅጣጫው ሸሸ። ይሄኔ ነው በሰዎች ህየወትና አካል ላይ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ ያጋጠመው። በተለይ ወደሃይቁ አቅራቢያ ያፈገፈጉ ሰዎች ውስጥ ለውጥ በውሃ የተበላ መሬት ላይ በመውጣታቸው ተደርምሶ ወደገደል ወድቀው የበርካቶች ህይወት ጠፍቷል። በሽሽት ላይ ወድቀው በመረጋገጥ የሞቱም አሉ። ይህን ጽሁፍ እስከማዘጋግበት ግዜ ድረስ ባለኝ መረጃ የሟቹቹ ቁጥር 55 ሲሆን የቆሰሉት ደግሞ መቶ ናቸው። ከቆሰሉት ውስጥ 97ቱ ህክምና ተደርጎላቸው ወደቤታቸው ተመለሰዋል።
እንግዲህ የምስጋና፣ የሰላም፣ የደስታና የማህበራዊ ትስስር መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል ሆን ተብሎ እልቂት እንዲያስከትል ታስቦ በእነጃዋር በተቀነባበረ ሁከት ተቋርጦ በሃዘንና በለቅሶ ድባብ እንደተዋጠ፤ የጋዋር እንዲሁም ሌሎች የኤርትራ መንግስት የሚመራቸውና በግብጽ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የፌስ ቡክ ላንቃዎች ተከፈቱ። በኢሬቻ በዓል ላይ የተነሳ ተቃውሞን ለማክሸፍ የመንግስት ወታደሮች ከሄሊኮፕተርና ከምድር በከፈቱት ተኩስ 500 ሰዎች ተጨፈጨፉ እያሉ ሰሞኑን በሃገሪቱ የሰፈነው ሰላም ያሳጣቸውን የሞትና የጥላቻ ወሬ ጥማት ሃራራቸውን ተወጡ።  በየደቂቃው እየተቀባበሉ የእልቂት ዜናቸውን የሚዲያ ስነምግባርነ በሚጥስ በአስከሬን ፎቶግራፍ የታጀበ ወረሬያቸውነ የነሰንሱ ጀመር። 
ቀደሞውኑ እልቂት ለመቀሰቀስና በመረጋገጥና ከገደል ላይ በመውደቅ ህይወታቸው ያለፈ የኢሬቻን በአለ ለማክበር በቦታው ተገኝተው የነበሩ ሰዎችን አስከሬን ፎቶ እየለጠፉ በጥይት ተደብድበው የተገደሉ እያሉ ቢያወሩም፣  በጥይት ተመቶ የሞተና የደማ አስከሬን ግን ማግኘት አልቻሉም። መልእክቱን የሚያስተላልፉት ብዙም ነገር ለማያገናዝቡ የማወክ ግን አቅም ላላቸው ለጋ ወጣቶች በመሆኑ በጥይት የተመታ ሰው ማሳየት ባይችሉም ብዙም አላሳሰባቸውም። አንድም የጥይት ድምጽ የማይሰማባቸውን ቪዲዮዎች ለጥፈው የመንግስት ሰራዊት ከምድርና ከሰማይ ህዝቡን ሲጨፈጭፍ የሚያሳይ ቪዲዮ እያሉ ሲለጥፉ ሃፍረት አልተሰማቸውም።
ይህ ሁኔታ ጃዋር መሃመድና ሌሎቸ በትምክህት ጎራ የተሰለፉ የኤርትራና የግብጽ ቅጥረኞች ለኦሮሞ ህዝብና ለባህሉ ደንታ የሌላቸው ያለምንም ሃፍረት ውሸት በማውራት የዋህ ወጣቶችን በማደናገር  ወደሞት እየነዱ ደማቸውን የሚቸረችሩ ርኩሶች መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል።
የሚገርመው የጃዋርና ሌሎች የኤርትራ መንግስትና ግብፅ ያሰማሯቸው የሁከት ላንቃዎች ተሳስተው እንኳን አንድ እውነት አላወሩም። በሞተ ሰው ልክ የሚከፈላቸው እነጃዋር የሟቾችን ቁጥር ከ500 በላይ አድርሰውታል። በኢሬቻ በአል ላይ በተቀሰቀሰው ሁከት በመውደቅና በመረጋገጥ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ግን ከዚህ ፍጹም የተለየ ነው። በዚህ ዙሪያ ያለውን መረጃ ከመንግስት ሃላፊዎች ሳይሆን ከሆስፒታል የተገኘ መረጃን ጠቅሼ ላሳያችሁ።
የቢሾፍቱ ሆስፒታል አደጋው በደረሰ በማግስቱ መስከረም 23፣ 2009 በሰጠው መግለጫ በኢሬቻ በዓል በተፈጠረ ሁከት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች  ቁጥር 55 መደረሱን አሳውቋል። ሁከቱ በተቀሰቀሰበት እለት በአደጋው ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ 54 ሰዎችን አስከሬን መቀበሉን ያሳወቀው ሆስፒታሉ፣ በማግስቱ አደጋው በደረሰበት ሆራ አርሰዲ በሚገኘው ገደላማ የተባለ ስፍራ የተገኘ አንድ አስከሬን መረከቡን አስታውቋል።  ሁሉም አስከሬኖች በሁከቱ ማግስት እስከ ተሰያት ባለው ግዜ ለቤተሰቦቻቸው ተሰጥተው ወደየመጡበት አካባቢ መወሰዳቸውንም ሆስፒታሉ ገልጿል። 
በአደጋው 100 ሰዎች ላይ ቀላል፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው ከእነዚህ ሰዎች መካከል 97-ቱ የህክምና አገልግሎት አግኝተውና ህክምናቸውን ጨርሰው ከሆስፒታል መውጣታቸውን አመልክቷል።  ሁለት ታካሚዎች በቢሾፍቱ ሆስፒታል፣ ሌላ አንድ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ታካሚም ወደ ሌላ የህክምና ተቋም ሪፈር ተመርተው በመታከም ላይ እንደሚገኝም ከሆስፒታሉ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።  
የሟቾቹን የሞት ምክንያት አስመልክቶ  የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አሰድ አህመድ መግለጫ ሰጥተዋል። ሟቾቹ በመረጋገጥ፣ በመታፈን፣ እርስ በርስ በተፈጠረ መተፋፈግ ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸውን እንዳጡ በምርመራ መረጋገጡን ነው ሜዲካል ዳይሬክተሩ ያስታወቁት። ከሟቾቹም ሆነ ከቁስለኞቹ መካከል አንድም ሰው በጦር አልያም በሌላ መሳሪያ ጉዳት የደረሰበት አለመገኘቱንም አረጋግጠዋል። የሞቱ ዋና ምክንያትም መረጋገጥ እና መታፈን ብቻ ነው ብለዋል ዶክተር አሰድ።
እንግዲህ የዘንድሮን የኢሬቻ በዓል ያለወጉ አውሎ ንጹሃን ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈ አስከፊ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ላይ መሪር ሃዘን ሲጥል፤ ለጃዋር፣ እንዲሁም ሌሎች የኤርትራና የግብፅ ቅጥረኞች ደገሞ ሲሳይ ሆኗል። 
በዚህ ምክንያት የኢፌዴሪ መንግስት የሶስት ቀናትተ የሃዘን ቀን አወጆ የማንነታችንና የኩራታችን መገለጫ የሆኑት የኢፌዴሪ ሰንደቃላማና የሁሉም ክልላዊ መንግስታት ሰንደቅዓላማዎች ዝቅ ብለው ተውለብልበው በሃዘን የተሰበረውን ልባችንን አመልክተዋል። የሞት ሲሳይ የወረደላቸው የጃዋር፣ የmereja.com፣ የEthiopian DJ እና የመሳሰሉ የኤርትራና የግብጽ ቅጥረኛ ማህበራዊ ሚዲያዎች ደግሞ ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸው በዘሩት ሞት ሲፈነጥዙ፣ ሃሰተኛ ወሬ እየነዙ ህዝብን ለሌላ መተላላቀና ሁከት ለማነሳሳት ሲቅበዘበዙ ቆይተዋል። የዘንድሮውን ኢሬቻ ያለወጉ ሃዘን እንዲያጠላበት ያደረገው ይህ እነጃዋር ከዶላር ጋር ተቀበለው የተሸከሙት እኩስ መንፈስ ነው። የረኩስ መንፈሱ መድሃኒት እኛ ጋር ነው ያለው። ቀዳሚው ፈውስ በዚህ በኢሬቻ በአል ላይ የታየውን የኦሮሞን ባህልና ወግ፣ ማንነት የሚያዋርድ ድርጊት መገንዘብ ነው። ኦሮሞዎች ባህልና ወጋቸውን ያሚያዋርድ፣ ማንነታቸውን የሚያንቋሽሽ ወዳጅ ሊኖራቸው ስለማይችል የጃዋርን ማንነት ይረዳሉ። ሰሞኑን ሲያወራ የነበረው ሙልጭ ያለ ውሸት ዓላማ ኦሮሞዎችን እርስ በርስና ከሌሎች ጋር በማጋጨት ሃገሩን በገዛ እጁ እንዲያፈርስ ማድሬግ ነው። ይህ  ደግሞ ከግብጽና ከኤርትራ ከዶላር ጋር የተሰጠው ዓላማ ነው። ኢሬቻን የበላው ርኩሰ መንፈስ ይሄ ነው። ርኩስ መንፈሱ ሰላማችንን በልቶ ደሃና ደካማ ሳያደርገን በፊት እንከላከለው።